የእስፓኝ እና የጣሊያን የእግር ኳስ ጨዋታ

ታዲያስ! ሮዜር እባላላሁ። የአማርኛ ተማሪ እና የእስፓኝኛ ቋንቋ አስተማሪ ነኝ። አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ጦማር እጽፋለሁ።

ትላንት ማታ የእግር ኳስ ጨዋታ “አፍሪካና” ካፌ ዉስጥ አየሁ። ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች በካፌው ውስጥ እያዩ ነበር። ሁሉም የጣሊያን ደጋፊዎች ነበሩ። በጨዋታው ጣሊያን እስፓኝን ሁለት ለዜሮ አሽነፈ። እነሱ በዚህ በጣም ተደሰቱ። እኔ በእግርኳስ ግጥሚያው ጊዜ በአንድ ነገር ተገረምኩ፡፡ ምክንያቱም የተጫዋቾቹ ስም በጣም በተለየ ሁኔታ እየተጠራ ነበር። ለምሳሌ አንድ የእስፓኝ ጎል ጠባቂ ስም De Gea (ዴሄአ) ሲሆን ፣ ጋዜጠኛው ግን “ዲጄያ” በማለት እየጠራው ነበር።

ይህን ከሰማሁ በኋላ እኔ  ስለእስፓኝኛ ቋንቋ አነባበብ ትንሽ መናገር ፈለግኩ።

እስፓኝኛ ቋንቋ እንደ አማርኛ ፎኔቲክ አነባበብ አለው። አምስት ዋና ድምፆች አሉት፡፡ እነሱም፥

a (አ፣አራተኛ)፣

e (ኤ፣አምስተኛ)፣

i (ኢ፣ሶስተኛ)፣

o (ኦ፣ሰባተኛ)፣

u (ኡ፣ሁለተኛ)።

ለምሳሌ፥

da, de, di, do, du (ዳ፣ ዴ፣ ዲ፣ ዶ፣ ዱ)፣

ba, be, bi, bo, bu/ va, ve, vi, vo, vu (ባ፣ ቤ፣ ቢ፣ ቦ፣ ቡ)፣

na, ne, ni, no, nu (ና፣ ኔ፣ ኒ፣ ኖ፣ ኑ)፣

ña, ñe, ñi, ño, ñu (ኛ፣ ኜ፣ኚ፣ ኞ፣ ኙ)።

ነገር ግን ከእነዚህ ትንሽ ከበድ ያሉ ድምፆችም አሉ።

za, ce, ci, zo, zu (ሳ፣ ሴ፣ ሲ፣ ሶ፣ ሱ)፣

ga, gue, gui, go, gu (ጋ፣ ጌ፣ ጊ፣ ጎ፣ ጉ)፣

ca, que, qui, co, cu (ካ፣ ኬ፣ ኪ፣ ኮ፣ ኩ)፣

ha, he, hi, ho, hu (አ፣ኤ፣ኢ፣ኦ፣ኡ)።

ለምሳሌ የኩባዊው ጀግና ስም Che Guevara (ቼጌባራ) እንጂ “ቼጉቬራ” አይደለም።

በተመሳሳይ ሌሎች ስምች እንደ David Villa (ዳቢት ቢያ)፣ Iniesta (ኢኒኤስታ)፣ Sergio Ramos (ሴርሂኦ ራሞስ)፣ Casillas (ካሲያስ)፣ David Silva (ዳቢት ሲልባ)፣ Santi Cazorla (ሳንቲ ካሶርላ)፣ Juan Mata (ሁኣን ማታ) … ተብለው ይነበባሉ፡፡

Gerard Pique (ጄራርት ፒኬ) እና Xavi (ሻቪ) ካታላናዊ ሰሞች ናችው።

ይህ ስለእስፓኝኛ ቋንቋ በጣም ጥቂቱ ነው። የበለጠ ለማወቅ ከፈለጋችሁ፣ ልታሳውቁኝ ትችላላሁ።

አመሰግናለሁ!

Anuncios

2 thoughts on “የእስፓኝ እና የጣሊያን የእግር ኳስ ጨዋታ

Responder

Introduce tus datos o haz clic en un icono para iniciar sesión:

Logo de WordPress.com

Estás comentando usando tu cuenta de WordPress.com. Cerrar sesión / Cambiar )

Imagen de Twitter

Estás comentando usando tu cuenta de Twitter. Cerrar sesión / Cambiar )

Foto de Facebook

Estás comentando usando tu cuenta de Facebook. Cerrar sesión / Cambiar )

Google+ photo

Estás comentando usando tu cuenta de Google+. Cerrar sesión / Cambiar )

Conectando a %s